በኤርትራ ላይ የተጠናከረው ማዕቀብ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 26 2004ማስታወቂያ
ምክር ቤቱ ትናንት ባስተላለፈው የተጠናከረ የማዕቀብ ውሳኔ መሠረት፡ በሶማልያ ለሚንቀሳቀሱ አሸባሪዎች ከለላ ሰጥተዋል ባላቸው በርካታ የኤርትራ ባለሥልጣናት እና ተቋማት ላይ የንብረት እና የጉዞ ዕገዳ ጥሎዋል። ኤርትራ ከአል ቓይዳ ጋ ግንኙነት አለው ለሚባለው አክራሪ የሶማልያ ዓማፅያን ቡድን አል ሸባብ የገንዘብና የትጥቅ ድጋፍ እንደምትሰጥ የተመድ ገልፆዋል። በናይጀሪያ እና በጋቦ አርቃቂነት የቀረበውን ይህንኑ ማዕቀብ አስራ ሶስቱ አባል ሀገሮች ሲደግፉት፡ ሩስያ እና ቻይና ድምፅ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ይሁንና፣ ኤርትራ የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የጣለባትን ተጨማሪ ማዕቀብ ፍትህ የጎደለው ሕገ ወጥ ነው ስትል በጥብቅ በመቃወም ውሳኔውን እንደማትቀበለው ቀደም ሲል በስልክ ያነጋገርኳቸው የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር አቶ አሊ አብዱ አስታውቀዋል።
አበበ ፈለቀ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ