በኤርትራ ላይ የቀረበው የሰብዓዊ መብት ረገጣ ወቀሳና ማስተባበያው
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 8 2001ማስታወቂያ
ዘገባው እንዳመለከተው፡ የኤርትራ መንግስት ዜጎቹን ለከፍተኛ ስቃይ፡ ሰቆቃ፣ ለእስርና ለተራዘመ የብሄራዊ ውትድርና ዳርጎዋል። ስለዚሁ ወቀሳ አበበ ፈለቀ የድርጅቱን የአፍሪቃ ጉዳይ ተመልካችን ሌስሊ ሌፍኮውን አነጋግሮዋቸዋል። የአሥመራ ወኪላችን ጎይትኦም ቢሆን ያነጋገራቸው የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ፍስሀጽዮን ጴጥሮስ ለዶይቸ ቬለ በሰጡት ቃለምልልስ የ« ሂውመን ራይትስ ዎች » ወቀሳ በኤርትራ በኩል ውድቅ መሆኑን አስታውቀዋል።
አበበ ፈለቀ /ጎይትኦም ቢሆን /አርያም ተክሌ/ሸዋዬ ለገሠ