1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢኦተቤክ የሰንበት ት/ቤቶችና የሲኖዶሱ ጉባኤ

ሐሙስ፣ ግንቦት 25 2003

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን፣ የሰንበት ት/ቤት ማደራጃ መምሪያ መግለጫ አዉጥቷል ።

https://p.dw.com/p/RRR2
ምስል DW

በመግለጫዉ ምንም እንኳን ማኅበረ ቅዱሳን፤ የተባለዉ ማኅበር በተለያዩ ዘርፎች የቤተክርስቲያኒቱ ረዳት ቢሆንም፤ የመምሪያ ኀላፊ የሚፈጽማቸው ግድፈቶች አሉ ብለዋል። ግድፈቱ ምንድን ነው? የመምሪያው ኀላፊ ስለሰጡት መግለጫ፤ ማኅበረ ቅዱሳን ምላሽ መስጠቱን ጌታቸው ተድላ አጠናቅሮ የላከልን ዘገባ ያስረዳል።

በተጨማሪም የ ኢ ኦ ተ ቤ/ክርስቲያን ጠቅላይ ሲኖዶስ ፤ ለ አንድ ሳምንት በዘለቀው በቤተ/ክርስቲያኒቱ ውስጥ፤ ታደሰ እንግዳው በላከልን ዘገባ ላይ እንዳለው፣ ተፈጠረ በተባለው አፈንጋጭ የተሃድሶ እምነት እንቅሥቃሴ ላይ ፤ ረጅም ጊዜ የፈጀና ያለስምምነት የተቋጨ ድምድሜ ላይ ደርሷል። የሲኖዶሱ ጉባዔ ፣ በእንዲህ ሁኔታ መደምደሙን ለዶቸ ቨለ ያስታወቁት ፣ ዘጋቢአችን እንደጠቀሰው ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አባቶች ናቸው።

ጌታቸዉ ተድላ

ታደሰ እንግዳዉ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ