በኢትዮጵያ የሚሞቱ ህጻናት ቁጥር መቀነስ
ዓርብ፣ መስከረም 10 2006
ባሁኑ ወቅት 68 መሆኑን የተመድ የህጻናት መርጃ ድርጅት (UNICEF)አስታዉቋል። ከ 20 ዓመት በፊት ከ 5 ዓመት በታች በሆነ ዕድሜ ውስጥ የሚሞቱ ከ 1000 - 200 እንደነበርም ተመልክቶአል። በኢትዮጵያ የሟች ህጻናት ቁጥር መቀነሱን በተመለከተ፤ የዶቼ ቬለዋ ሳንታ ብሎመን ከተመ የህጻናት መርጃ ድርጅት ቃል አቀባይ ጋር ተነጋግራ የዘገበችዉን አዜብ ታደሰ እንዲህ ታቀርበዋለች፤
«በኢትዮጵያ ብቻ በዓመቱ የ200,000 ህጻናት ህይወት ተርፎአል፤ በጣም ትልቅ ቁጥር ነዉ»
በኢትዮጵያ ያለዉ የህክምና ሁኔታ የተሟላ የሚባል አይደለም። እንድያም ሆኖ በሀገሪቱ የታየዉ የጤና አጠባበቅ ጉዳይ አበረታች ያለዉ፤ የተመ የህጻናት መርጃ ድርጅት፤ ለዉጡን አብዮታዊ ብሎታል። ለዉጡ በተለይ በአንድ ጉዳይ ላይ ወሳኝ ነበር ይላሉ፤ በተመ የህጻናት መርጃ ድርጅት ቃል አቀባይ ሻንታ ቢሎመን፤
«በርግጥም መንግስት በሀገሪቱ ያለዉን መሰረታዊ የጤና ክትትል ላይ ገንዘብ አፍስሶአል። መዋለ ንዋይ የማፍሰሱ ዋጋ ደግሞ ህይወታቸውን የሚያጡ ህጻናት ቁጥር መቀነሱ ነዉ።»
የኢትዮጵያ መንግስት ትኩረቱን ያደረገዉ በአብዛኛዉ፤ በገጠሩ አካባቢ ላይ ነዉ። በጎአ 2003 ዓ,ም በሀገሪቱ ያሉትን፤ በተለይም በአካባቢ መሰረታዊ የጤና ጥበቃ ክትትልን ለማሻሻል ዉሳኔን ማሳለፉ ይታወሳል። በበርካታ የአፍሪቃ ሀገራት የህክምና ተጠቃሚዎች በአብዛኛዉ የከተማ ንዋሪዎች ብቻ በመሆቸናዉ ዉሳኔዉን ያልተለመደ አድርጎታል።
«የኢትዮጵያያ መንግስት 38,000 የጤና ጥበቃ ሰራተኞችን ረዘም ባለ ትምህርት ለአንድ ዓመት አሰልጥኖአል። ከዚህ በተጨማሪ የህክምና አገልግሎቱ በትክክለኛ እና ጥሩ ባለሞያዎች እንደሚካሄድ ክፍያ እንዲኖረዉም አድርጎአል»
በገጠሩ አካባቢ በየቀበሌዉ ዉጤቱ፤ የህክምና ሞያን የሚያዉቁ እና አንድ ሕጻን ለሞት የሚያበቃዉን በሽታ ምንነት በማወቅ ህክምና የሚሰጡ፤ ቢያንስ ሁለት የህክምና ባለሞያዎች እንዲኖሩ ሆንዋል። ህጻናቱ ከሚጠቁባቸዉ በሽታዎች መካከል ደግሞ የተቅማጥ፤ የሳንባ እና የወባ በሽታዎች ይገኙበታል። ከዚህ በተጨማሪ የህክምና ባለሞያዎቹ በአካባቢዉ ለሚኖረዉ ማህበረሰብ፤ በመኝታ ግዜ የወባ መከላከያ አጎበር እንዲያደርግ በየግዜዉ ትምህርት ይሰጣሉ። ሌሎች የአፍሪቃ ሀገራት በኢትዮጵያ የታየዉን አመርቂ ስራ በምሳሌነት በመዉሰድ በየሀገሮቻቸዉ ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት ላይ ይገኛሉ። ሊሎች የአፍሪቃ ሀገሮች በተለይ በገጠሩ አካባቢ በሚገኙ አካባቢዎቻቸዉ ላይ የጤና ሞያ ስልጠና መስጠት ጀምረዋል። እንድያም ሆኖ በጤና ጥበቃ ረገድ አህጉሪቱ ገና ብዙ መሥራት ይኖርበታል። እንደ ተ መ የህጻናት የአስቸኳይ ሁኔታ መርጃ ድርጅት ዘገባ በአፍሪቃ አህጉር ከአምስት ዓመት እድሜ በታች ያሉ ህጻናት፤ በየዓመቱ በቀላሉ በሚድን በሽታ ወደ አምስት ሚሊዮን ህጻናት ይቀጠፋሉ።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ