1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«በኢትዮጵያ ቢያንስ 140 ሰዎች ተገድለዋል» ሂውማን ራይትስ ዎች

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 29 2008

ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች «የታዋቂ ፖለቲከኞች መታሰር በኢትዮጵያ ቀውሱን እያባባሰው ነው» የሚል መግለጫ ትናንት አውጥቷል።

https://p.dw.com/p/1HaSK
Menschenrechte Logo human rights watch

[No title]

የኢትዮጵያ መንግሥት «የአዲስ አበባ የተቀናጀ ማስተር ፕላን» ያለውን ዕቅድ በመቃወም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ካለፈው ወር አንስቶ ለ1 ወር ሲደረግ የነበረው የአደባባይ ሰልፍ ወደ ግጭት አምርቶ የሰው ሕይወት አጥፍቷል። ሂውማን ራይትስ ዎች በትናንቱ መግለጫ የሟቾቹ ቁጥር ከዚህ ቀደም ከጠቀሰው በእጥፍ እንደሚጨምር ገልጧል። የሟቾቹን ቁጥር በተመለከተ መንግሥት እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ከዚህ በፊት እጅግ የተራራቀ ቁጥር ተናግረዋል። የኦሮሞ ፌዴራሊስ ኮንግሬስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ዳግም መታሰር እና ያሉበት ቦታ አለመታወቅ እንዳሰጋው የጠቀሰው መግለጫ፤ ቀውሱን ለመፍታት መፍትኄ ያለውንም ሐሳብ አቅርቧል። ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማን ከኬንያ አነጋግሬው ነበር። የሟቾቹ ቁጥር ምን ያኽል እንደሆነ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ የገለጠውን በማስቀደም ይጀምራል።

ፋሲል ግርማ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ