1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢራቅ ወረራ የብሪታኒያ ሚና ይፋ ምርመራ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 15 2002

አሜሪካ እና ብሪታኒያ ሌሎች አጋሮቻቸውን በማስተባበር ወደ ኢራቅ ጦር ካዘመቱ ከስድስት ዓመት በላይ ተቆጥሯል ። አሜሪካን መራሹ ይህ ወራራ እስካሁን ውዝግብ ሳይለየው እንደዘለቀ ነው ።

https://p.dw.com/p/KeRg
የኮሚሽኑ ሀላፊ Sir John Chilcotምስል picture alliance / empics

በኢራቅ ጅምላ ጨራሽ የጦር መሳሪያ አለ ተብሎ ጦርነቱ ቢጀመርም ኃላ ላይ የተባለው መሳሪያ አለመገኘቱ የወረራውን ህጋዊነት አጠያያቂ እንዳደረገው ነው ። በነዚህና በሌሎችም መልስ ያስፈልጋቸዋል በተባሉ ከኢራቅ ጦርነት ጋር በተያያዙ ነጥቦች ላይ በብሪታኒያ የኢራቅን ወረራ የፈቀዱትን የብሪታኒያ ባለስልጣናትን የጦር ዕርምጃ ህጋዊነት ለማጣራት አንድ የብሪታኒያ ገለልተኛ ኮሚሽን ዛሬ ስራውን ጀምሯል ። ድልነሳ ጌታነህ ከለንደን ዝርዝሩን አዘጋጅቷል ።

ድልነሳ ጌታነህ ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ