1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢሕአዴግ መግለጫ ላይ የተቃዋሚዎች አስተያየት

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 23 2010

ኢሕአዴግ እራሱ አምኖ በተቀበላቸው ድክመቶቹ ሀገሪቱን መምራት ስለማይችል ሥልጣን መልቀቅ ነበረበት ሲሉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጡ ። ኢሕአዴግ አኹን ሀገሪቱን መምራት በማይችልበት ደረጃ እንደደረሰም ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/2qBe7
Äthiopien vor der Wahl EPRDF Anhänger in Addis Abeba
ምስል Getty Images/AFP/Z. Abubeker

ኢሕአዴግ «ሀገሪቱን መምራት ስለማይችል ሥልጣን መልቀቅ ነበረበት» ተቃዋሚዎች

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) እራሱ አምኖ በተቀበላቸው ድክመቶቹ ሀገሪቱን መምራት ስለማይችል ሥልጣን መልቀቅ ነበረበት ሲሉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች  ገለጡ።  የሰሞኑ ስብሰባውም ግንባሩን ለማዳን እንጂ ለሕዝቡ የፈየደው ነገር የለምም ብለዋል። እንዲያም ሆኖ ግንባሩ ከኹለት ሳምንት በላይ በዝግ ያከናወነውን ስብሰባ ሲቋጭ ባወጣዉ መግለጫ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓቱን ለማጎልበት ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች ማሳተፍ አማራጭ የለዉም ማለቱን በአዎንታዊ ያጠቀሱም አሉ። የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን በማነጋገር የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።


ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ