1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአፍጋኒስታን የተማረከው የአሜሪካን ወታደር

ሰኞ፣ ሐምሌ 13 2001

የአሜሪካን ጦር በአፍጋኒስታን ውስጥ በታሊባን ቁጥጥር ስር የዋለው ወታደር ቃሉን የሰጠበት ቪድዮ በመረጃ መረብ መሰራጨቱ ዓለም ዓቀፍ ህግን የሚጥስ ተግባር መሆኑን አስታውቋል ።

https://p.dw.com/p/ItMK
ምስል picture-alliance/ dpa

ወታደሩ በታሊባኖች እንደተለቀቀ በተነገረው ቪድዮ ላይ የአሜሪካንን ወታደሮች የውጊያ ፍላጎት እንደቀነሰ ጠቁሞ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ፣ የአሜሪካን ህዝብ እንዲታደጋቸው ጠይቋል ። የፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ አዲስ የማጥቃት ስትራቴጂ እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካ ወታደር ታግቶ ቃሉን ሲሰጥ ለዕይታ የበቃው ከትናንት በስተያ ነው ። አበበ ፈለቀ ዝርዝር ዘገባ አለው ።

አበበ ፈለቀ ፣ ሂሩት መለሰ/አርያም ተክሌ