በአፋር ክልል የተሰረቀው የርዳታ እህል ጉዳይ 11 ሚያዝያ 2004ሐሙስ፣ ሚያዝያ 11 2004ከለጋሽ ሀገሮች የሚገኘውን የርዳታ እህል ለተረጂዎች በአግባቡ እንዲደርስ መንግሥት ጠንካራ ቁጥጥር እንዲያደርግ ተጠየቀ። ይህ ጥያቄ ሊቀርብ የቻለው ሰሞኑን በአፋር ክልል ዞን ሶስት ከአዋሽ ሸለቆ መጋዘን ወደ ሀረር ድሬዳዋ ይጓጓዝ የነበረ የርዳታ እህል በመንገድ ከተሰረቀ በኋላ ነው።https://p.dw.com/p/14hDbምስል picture-alliance/dpaማስታወቂያ በስድስት የጭነት ተሽከርካሪዎች ሲጓጓዝ ሳለ የተሰረቀው የእህል ርዳታ በፖሊስ ቁጥጥር የዋለው በሕዝብ ጥቆማ እንደነበር የድሬዳዋ ዘጋቢያችን ዮሀንስ ገብረእግዚአብሄርያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር አርያም ተክሌ ነጋሽ መሐመድ