በአጅ ያለውን ጠንቅቀው ሳያውቁ፣ መጓዝ ወደሩቁ፣11 የካቲት 2001ረቡዕ፣ የካቲት 11 2001በሚል ርእስ በዘንድሮው የሥነ ፈለክ መታሰቢያ ዘመን ፣ ከፀሐያዊ ጭፍሮች ባሻገር ያለውን ፣ በሚመጥቁ መንኮራኩሮች አማካኝነት ለማወቅ ስለሚደረገው ጥረት ይሆናል፤ በዛሬው ሳይንስና ኅብረተሰብ ቅንብራችን ይበልጥ የምናተኩረው።https://p.dw.com/p/Gwsoጀርመናዊው የሥነ ፈለክ ተመራማሪና የሂሳብ ሊቅ፣ ዮሐንስ ኬፕለር፣ እ ኤ አ፣ከ(1571-1630)ምስል dpaማስታወቂያበኅዋ ፣ የተለያዩ ከዋክብትና ፕላኔቶችን ፣ አቀማመጣቸውንና ከፀሐይ ያላቸውን ርቀት ለማወቅ፣ ዘመናዊው የሥነ ፈለክ ምርምር ከተጀመረ 400 ዓመት ሆኖታል። ይሁንና፣ በዚሁ የሥነ ፈልክ ምርምር ረገድ ፣ መሪ ሚና በመያዝ ገለጣ ያደርጉ የነበሩ ተመራማሪዎች ፣ ብርቱ ፈተና ፣ በህይወታቸውም ላይ ከባድ አደጋ ያንዛብብባቸው እንደነበረ የሚካድ አይደለም። T Y