1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአውሮፓ ፀረ ሽብር እንቅስቃሴና ክትትሉ

ዓርብ፣ ግንቦት 21 2001

እንደ ጎሮጎሮሳውያን ዘመን አቆጣጠር ከመስከረም አስራ አንድ ሁለት ሺህ አንዱ የአሜሪካን የአሸባሪዎች ጥቃት ወዲህ በአውሮፓ አሸባሪነትን ለመከላከል መንግስታትና ህግ አስፈፃሚዎች የሚወሰዷቸው ዕርምጃዎች የውጭ ዜጎችን ለአድልዎ ከማጋለጡና ከማግለሉ ውጭ ምንም ዓይነት ውጤት አለማምጣታቸው ሰሞኑን ይፋ ሆኗል ።

https://p.dw.com/p/HzfG
ሙስሊሞች በበርሊን መስጊድምስል AP

በህብረተሰቡ ውስጥ ግልፅ አሰራርና ፍትህ እንዲሰፍን በሚጥረው Open Society Institute በተባለው የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ቡድን ስር የፍትህን ጉዳይ የሚከታተለው ክፍል ፣ በአምስት የአውሮፓ አገራት ያካሄደውን ጥናት መሰረት በማድረግ በዚህ ሳምንት ማክሰኞ ባወጣው ዘገባ እንደጠቆመው ፣ የአንዳንድ የአውሮፓ መንግስታት ፀረ አሸባሪነት መርህ ንፁሀን ሰዎችን ከማንገላታቱና ሰብዓዊ መብታቸውን ከመጋፋቱም በላይ እነዚህ የህብረተሰብ ክፎሎቸ በፀረ ሽብሩ ዕንቅስቃሴ ከፖሊስ ጋር ሊተባበሩ የሚችሉበትን መንገድም ዘግቷል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ