የአቶ ዮናታን ክስ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 28 2008ማስታወቂያ
ዛሬ ያስቻለው የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19 ነኛ ወንጀል ችሎት የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዮ በተከሰሱበት የፀረ ሽብር ህግ እንዲከላከሉ ብይን ሰጠ ። ችሎቱ አቶ ዮናታን የተከሰሱባቸው ጽሁፎች ፣የመናገር ነጻነት ላይ የተደረጉ ክልከላዎችን እና የፀረ ሽብሩን አዋጅ 652 /2001 አንቀጽ 4 ን የሚተላለፉ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ ብሏል ። ፍርድ ቤቱ አቶ ዮናታን የመከላከያ ምስክሮች ይዘው እንዲቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ። ችሎቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ