1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአባይ ተፋሰስ ላይ የተካሄደ ዐውደ ጥናት

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 23 2006

ብሉ ናይል በተባለው ተቋም አማካይነት በአባይ ላይ የተሰሩ ምርምሮችን በማሰባሰብ ተማራማሪዎችና ፖሊሲ አውጭዎችና መረጃውን የሚፈልጉ የተለያዩ አካላት እንዲያገኙት ለማስቀመጥ ተሞክሯል ።

https://p.dw.com/p/1Bs6C
Treffen von Staatschefs in Bahir Dar, Äthiopien
ምስል DW/G.Tedla-Haile-Georghis

ስለ አባይ ወንዝ አጠቃቀምና ስለ ህዳሴው ግድብ በእውቀት ላይ የተመሰረተ መረጃ የሚቀርብበት ስ

ርዓት መዘርጋቱ ተገለጠ ። የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ባይሌ ዳምጤ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ስር በተቋቋመው ብሉ ናይል በተባለው ተቋም አማካይነት በአባይ ላይ የተሰሩ ምርምሮችን በማሰባሰብ ተማራማሪዎችና ፖሊሲ አውጭዎችና መረጃውን የሚፈልጉ የተለያዩ አካላት እንዲያገኙት ለማስቀመጥ ተሞክሯል ። ተቋሙ በአባይ ውሃ ላይ ተጨማሪ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ በመስኩ ያለውን እውቀት ለማሳደግ በመጣር ላይ መሆኑንም አስታውቀዋል ። ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን በአባይ የውሃ ሃብት ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ በተወያዩበት የሁለት ቀናት ስበሳባ ላይ ዶክተር ባይሌንና ሌሎች ተሳታፊዎችን ያነጋገረው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኅይለ ጊዪርጊስ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።

ጌታቸው ተድላ ኅይለ ጊዪርጊስ

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ