1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአሸባሪነት የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ችሎት

ሐሙስ፣ ጥቅምት 23 2004

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት የፌዴራሉ ዓቃቤ ሕግ በሽብር ድርጊት ዋና ተሳታፊ በመሆን አራት የተለያዩ ክሶች በመሰረተባቸው ሁለት ኢትዮጵያውያን እና ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞች ላይ ዛሬ የተለያየ ብይን ሰጥቶዋል።

https://p.dw.com/p/Rugu
ምስል Fotolia/Werner Schwehm

ችሎቱ ሁለቱ የኦብነግ አባላት ከተመሰረቱባቸው ሁለት ክሶች በአንደኟው ጥፋተኛ ናቸው ሲል በይኖዋል፤ ሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ደግሞ ከተመሰረቱባቸው ሦስት ክሶች በሁለቱ እንዲከላከሉ በይኖዋል። የስዊድናውያኑ ጠበቆች ምስክሮች ለማቅረብና ማስረጃዎቻቸውን ለማደራጀት ጊዜ በመጠየቃቸው ፍርድ ቤቱ ሕዳር ሀያ ስድስት ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶዋል። ታደሰ እንግዳው

ታደሰ እንግዳው

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ