በናይጀሪያ የነዳጅ ዘይት ዋጋ መናር ያስከተለው ተቃውሞ
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 26 2004ማስታወቂያ
ድጎማው ከተነሳ በኋላ የነዳጅ ዘይት ዋጋ በእጅጉ መናሩ ናይጀሪያውያንን አስቆጥቷል ። ህዝቡ ኃይል የተቀላቀለበት የተቃውሞ ሰልፍ ከማካሄድ አንስቶ ካኖን በመሳሰሉ ከተሞች የነዳጅ ማደያዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ እስከ ማድረግም ደርሷል ። ዋነኛው የናይጀሪያ የሰራተኛ ማህበርም በሚቀጥለው ሳምንት በመላ ሃገሪቱ የስራ ማቆም አድማ እንደሚጠራ ዝቷል ። ተቃውሞው በተባባሰበት በሰሜን ናይጀሪያ አንዳንድ አካባቢዎች መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ ደንብ ደንግጓል ።
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ