1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ የባቡር መስመር ዝርጋታ መሰረዙ ያስነሳዉ ቁጣ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 26 2009

የመቐለ ሽረህ ሃሞራ የባቡር መስመር ተቋርጦአል መባሉ በነዋሪዉ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን መቀስቀሱ ተሰማ። አረና ትግራይ በበኩሉ የፊደራል መንግሥት ትግራይን በፖለቲካም በኤኮኖሚም እያገለላት ነዉ ብሎአል።

https://p.dw.com/p/2cONO
Äthiopien 40. Jahrestag TPLF
ምስል DW/T. Weldeyes

Ber. A.A (Protest gegen Hailemariams Aussage in Tigray) - MP3-Stereo

 አድዋ ላይ ይገነባል የተባለዉን የፓን አፍሪቃ ዩንቨርስቲ የመሠረት ድንጋይ ያኖሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን ከነዋሪዉ ጋር ባደጉት ዉይይት የባቡር ሥራ ግንባታዉ በኛ እድሜ የሚፈፀም አይደለም በማለታቸዉ ከሕዝብ ከፍተኛ ትችት እየተሰነዘረባቸዉ መሆኑም ተመልክቶአል። አረና ትግራይ በበኩሉ የፊደራል መንግሥት ትግራይን በፖለቲካም በኤኮኖሚም እያገለላት ነዉ ብሎአል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አገደን እንጂ ትግራይ በሰላማዊ ሰልፍ ትናጥ ነበርም ሲል መግለፁን ወኪላችን የላከልን ዘገባ ያመለክታል። 


ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ