1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቱርክ የጀርመን ተቋማት መዘጋት

ሐሙስ፣ መጋቢት 8 2008

ጀርመን በቱርክ መዲና አንካራ እና በኢስታንቡል የሚገኙትን ኤምባሲዋን እና ቆንስላ ጽህፈት ቤት፣ እንዲሁም በሁለቱ ከተሞች የሚገኙትን የጀርመን ትምህርት ቤቶችና ተቋማት ዛሬ ዘጋች። የጀርመን ፀጥታ መስሪያ ቤት የሽብር ጥቃት እቅድ መኖሩን የሚያመላክት ተጨባጭ ማስረጃ እንደደረሰው የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፍራንክቫልተር ሽታይንማየር አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/1IEjZ
Deutsche Botschaft in Ankara Türkei
የጀርመን ኤምባሲ በአንካራምስል picture-alliance/dpa/B.Wüstneck

[No title]

የኢስታንቡል ባለስልጣናት በጀርመን ውሳኔ ቅር መሰኘታቸውን ገልጸዋል፣ የቱርክ ጠቅላይ ሚንስትር አህመት ዳቮቱጉሉ ግን የጀርመን መንግሥትን ስጋት እንደሚረዱት አስታውቀዋል። የፀጥታ መስሪያ ቤቱ ባለስልጣናት ምን ዓይነት ማስረጃ ነው ያገኙት? ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የተገኘ ማብራሪያ አለ ወይ? ተቋማቱ እስከ መቼ ተዘግተው ይቆያሉ? ጀርመን በቱርክ ያሉትን ቋሚ ተልዕኮዎቿን እና ትምህርት ቤቶችዋን ከመዝጋት አልፋ በወቅቱ በተጨማሪ ምን ርምጃዎች ወስዳለች? በበርሊን የሚገኘውን ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤልን ቀደም ሲል በስልክ አነጋግሬው ነበር።

ይልማ ኃይለሚካኤል

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ