በቦስተኑ የቦንብ ጥቃትና ኢትዮ አሜሪካዊ ወጣት
ሐሙስ፣ ግንቦት 8 2005ማስታወቂያ
በቦስተን ማራቶን፤ የቦንብ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ፣ የአደጋ ጣዪው የዞኻር ዛርናዬብ ጓደኞች እንደሆኑ የተነገረላቸው 3 የኮሌጅ ተማሪዎች ግለሰቡን ተባብረዋል በሚል ክስ እንደተመሠረተባቸው የሚታወስ ነው። ግለሰቦቹ፤ በተለይ የሳርናየብ ርችቶች የተቀመጡበትን ቦርሳና ሌሎች ቁሳቁሶች ከሚኖርበት የአዳሪ ተማሪ መኝታ ክፍል በማሸሽና ለፌደራል የህግ አስፈጻሚ አካላት በመዋሸት መከሰሳቸው ሲነገር ቆይቷል። ከአነዚህ መካከል አንዱ ኢትዮአሜሪካዊው ወጣት ሮቤል ፊሊፖስ ሲሆን፤ ጠበቃው አቶ ደረጃ ደምሴ ሮቤል ከቦንቡ አደጋ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው ገልጸዋል።
አበበ ፈለቀ
ተክሌ የኋላ
አርያም ተክሌ