1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በብራዚል፣ ሉላ በአብላጫ ድምጽ ማሸነፍ

ሰኞ፣ ጥቅምት 20 1999

ብራዚል ዉስጥ በተደረገዉ ፕሪዝዳንታዊ የማጣርያ ምርጫ ፕሪዝዳንት ሉላ ከፍተኛ ድምጽ በማግኘት የሸናፊነቱን ቦታ ይዘዋል

https://p.dw.com/p/E0hp
አሸናፊዉ ፕሪዝደንት ሉላ
አሸናፊዉ ፕሪዝደንት ሉላምስል AP

ለሁለተኛ ግዜ በተደረገዉ በትናንትናዉ የፕሪዚደንታዊ የማጣርያ ምርጫ በስልጣን ላይ ያሉት ፕሪዚደንት ሉዊስ ኤናሲዮ ሉላ እና በተቀናቃኛቸዉ ጌራልዶ አልክሚን መካከል የተደረገ ሲሆን ፕሪዚደንት ሉላ 60.8 በመቶ ሲያገኙ ጌራልዶ አልክሚን ደግሞ 38.,2 በመቶ በማግኘት ተሸናፊ ሆነዋል።
የምርጫዉን ዉጤት ተናጋሪ፣ የቀድሞዉን እና በወቅቱ በድጋሚ የተመረጡትን የብራዚሉን ፕሪዚደንት ሉዊስ ኤናስዮ ሉላ ደ ሲልቫ አሸናፊነት ሲገለጽ፣ በየአደባባዩ ዉጤቱን ለመስማት ይጠባበቅ የነበረዉ የአገሪቷ ነዋሪ፣ በደስታ ጭብጨባዉን ማስተጋባት ጀመረ። አሸናፊነታቸዉን በሰሙ ግዜ፣ ለቀቅ ባለ ቲሸርት ላይ ጅንስ ጃኬታቸዉን አድርገዉ፣ ለጋዜጠኖች ቃለ ምልልስ ለመስጠት እና ደጋፊዎቻቸዉን ለማመስገን ወጥተዉ የታዩት ፕሪዚደንት ሉላ፣ በመቀጠልም ለምርጫዉ መሳካት ደጋፊዎቻቸዉን እንዲህ ሲሉ አመስግነዋል።
«ብራዚል መንግስት ላይ የታየዉን ተደገጋጋሚ ተጨባጭ ያልሆነ ጥርጣሪ፣ ሕዝቧ በአገሪቷ የሚካሄደዉን በእዉነት እና እዉነታን ያልያዘ ነገርን ማገናዘብ በመቻሉ እና፣ ይህንንም ማሳየት በማቻሉ የብራዚልን ህዝብ ማመስገን እወዳለሁ»
የ 61 አመቱ ፕሪዚደንት ሉላ የሁለተኛ የስልጣን ዘመናቸዉን ቢያስከብሩም፣ መስከረም መባቻ ላይ በተደረገዉ የመጀመርያዉ ዙር የፕሪዚደንታዊ ምርጫ ላይ የፈጸሙት ድምጽን የመግዛቱ ድርጊት ሃፍረት አለቀቃቸዉም። በዚሁ የተነሳ ከሶሻል ዲሞክራሲ አራማጁ እና፣ የሉላ ዋንኛ ተቀናቃኝ ከጌራልዶ አልክሚን የሚደርስባቸዉ የነበረዉ ትችት አጥንታቸ ሳይነካ አለቀረ። ያም ሆኖ ግን፣ ትናንት ከተደረገዉ የምርጫ ዉጤት በኳላ፣ ልክሚን ሽንፈታቸዉን በጸጋ ተቀብለዋል
«ዲሞክራሲ በእዉነቱ በጣም ታላቅ ነገር ነዉ፣ ለፕሪዚደንት ሉላን ስልክ ደዉዪ፣ ላገኙት ዉጤት እና አሸናፊነት እንኳን ደስ ያሎት ብያለሁ፣ ጥሩ ምኞቴንም አስተላልፊአለሁ። ይሄንንም ለአገራችን ለብራዚል እንፈልጋለን። በዚህ ወቅት ግን ለሶሻል ዶሞክራቶች ድልን ማግኘት ከባድ ሆንዋል»

የሰራተኞችን ፓርቲ የሚመሩት እና፣ ከደሃዉ ህብረተሰብ እንደመጡ የሚነገርላቸዉ ፕሪዝደንት ሉላ፣ በምርጫዉ ሶስት አራተኛዉን ድምጽ፣ ደሃዉ የአገሪቷ ህብረተሰብ ከሚኖርበት በተለይም፣ ከሰሜናዊ እና ከሰሜን ምስራቅ ብራዚል ክልል እንዳገኙ ታዉቋል። ባንጻሩ አልኪሚን በተለይ ባለጸጋዉ ህብረተሰብ ከሚኖርበት ክልል እንዳገኙ ነዉ የሚነገረዉ። ፕሪዚደንት ሉላ ለህዝባቸዉ ባሰሙት ንግግር ላይ፣
«በብራዚል ያለዉ የኑሮ ሁኔታ ተስተካክሎአል! የብራዚል ህዝብ ኪሱን እና የሚበላበትን ገበታ ሲያያየዉ የኑሮዉ ሁኔታ እንደትተካከለ ሳይረዳ አልቀረም»

የዛሪ አራት አመት ሉላ ስልጣን ላይ ለመዉጣት ለብራዚል ህዝብ ቃል የገቡትን ሁሉ ነገር ባይፈጽሙም በአብዛኛዉ የብራዚል ህዝብ የኑሮ ሁኔታ፣ ሉላ ስልጣን ከረገጡበት ግዜ ጀምሮ፣ በእዉነትም ቀለል ብሎአል። የሁለተኛ የስልጣን ዘመናቸዉን በጀመሩበት በትናንትናዉ እለትም በሚቀጥሉት አራት አመታት፣ በአገራቸዉ ድህነትን ለማጥፋት፣ የህብረተሰብ እኩልነትን ለማስፈን ከፍተኛ ትግል እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል። በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በጣም በዝቅተኛ ሁኔታ የሚራመደዉን የብራዚል ኢኮነሚን፣ የእድገቱ ፍጥነት እንዲጨምር የተቻላቸዉን እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
ፕሪዝደንት ሉላ በድምጽ ምርጫ መጭበርበር ጉዳይ በመጀመርያዉ ዙር ምርጫ ከፍተኛ ዉዝግብ ቢፈጠርም፣ ህዝቡ በድጋሚ በሉላ ላይ ያለዉን እምነት በመጣል፣ ለሁለተኛ ዙር የስልጣን ዘመን አብቅቶአቸዋል።