በቤንች ማጂ ዞን የማሌዥያ ኩባንያ ሠራተኞች አቤቱታ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 10 2006ማስታወቂያ
በቤንች ማጂ ዞን ማጂ ወረዳ በዘንባባ ዘይት ምርት የተሠማራ ኩባንያ ሠራተኞች «ደመወዝ ሳይከፈለንና ጥቅማ ጥቅሞቻችን ሳይሟሉ ከሥራ በመሰናበታችን ለችግር ተዳርገናል» ሲሉ አማረሩ። ሠራተኞቹ እንደሚሉት የአንድ ወር ደመወዝ አልተከፈላቸውም። የዞኑ ሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ በበኩሉ የሥራ ውሉ ሲቋረጥ በአዋጅ የሚገባቸውን ጥቅማ ጥቅሞች አሠሪው በ7 ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያሟላ ስምምነት ላይ መደረሱን አስታውቋል። ድርጅቱ ደግሞ በአዋጁ አተረጓጎም ላይ በሠራተኞቹ በኩል የግንዛቤ ችግር አለ ይላል። ሁሉንም ወገኖች ያነጋገረው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ