1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በባሕርዳር የቀጠለዉ አድማ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 3 2009

ባለፈዉ ሰሞን ቢሾፍቱ ከተማ  የኢሬቻን በዓል ለማክበር ተገኝተዉ ለሞቱት መታሰብያ እንዲሆን በሚል በባህርዳር ከተማ የተጠራዉ የአምስት ቀናት ከቤት አለመዉጣት አድማ እንደቀጠለ ቢሆንም፤

https://p.dw.com/p/2RCVu
Karte Äthiopien Amhara, Tigray, Oromia Deutsch

ዛሬ አንዳንድ ሱቆች መከፈታቸዉም የከተማዋ እንቅስቃሴም ከሰኞዉ ይልቅ የተሻለ መሆኑን የነገሩን የዓይን እማኞች ስማቸዉን እንዳንናገር ጠይቀዉናል። በሌላ በኩል በባህርዳር አገልግሎት ተቋርጧል አድማ ነበር የሚያሰኝ አልነበረም ያሉን የአማራ  ብሔራዊ መንግሥት ኮሚኒኪሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን፤ በመጀመርያ ቀን ሱቆች ተዘግተዉ ቢዉሉም በዛሬዉ እለት አብዛኞች ወደ ቀድሞ ስራቸዉ መመለሳቸዉን ተናግረዋል።  ሙሉዉን ቃለ ምልልስ የድምፅ  ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ