በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ የተከሰሱት ጉዳይ ችሎት
ረቡዕ፣ ጥር 24 2009ማስታወቂያ
በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ወቅት ለደረሰው የሰው እና የንብረት ጉዳት ተጠያቂ ናቸው ተብለው የተከሰሱት 38 ተከሳሾች ጉዳይ በዝግ ችሎት ይታይልኝ ብሎ አቃቤ ህግ ያቀረበው አቤቱታ ተቃውመው የተከሳሾቹ ጠበቀች መልስ ሰጡ ። ጠበቆቹ ዛሬ ለፉደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19 ነኛ ወንጀል ችሎት በጽሁፍ ባቀረቡት ምላሽ ዓለም አቀፍ ህጎችን ፣ የኢትዮጵያን ህገ መንግሥት እና ሌሎች ተዛማጅ ህጎችን በመጥቀስ ችሎቱ በግልጽ መታየት አለበት ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አስታውቀዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ