1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሶርያ የቀጠለው የኃይል ተግባር

ሐሙስ፣ ነሐሴ 5 2003

በተመድ የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የሚገኙ ምዕራባውያት ሀገሮች አምባሳደሮች በመንግስቱ ተቃዋሚዎች ላይ የኃይል ርምጃ ተጠናክሮ በቀጠለባት ሶርያ አንጻር ያለሙ መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ አካል ጠንካራ ርምጃ እንዲወስድ ጠየቁ።

https://p.dw.com/p/RfUz
ምስል Screenshot youtube

እንደሚታወሰው ምክር ቤቱ ቀደም ባለ ጊዚያት በዚህችው ሀገር በመካሄድ ላይ ያለውን የኃይል ተግባር አውግዞዋል። የዐረብ ሀገሮችም የሶርያ ፕሬዚደንት በሺር አል አሳድ የኃይሉን ተግባር እንዲያቆሙና የተሀድሶውን ለውጥ ባፋጣኝ እንዲያስተዋውቁ እያሳሰቡ ነው። የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱን ሶርያን ካወገዘበት ርምጃ የተቆጠበው የሊባኖስ መንግስት አቋምን የተቃወመው የሊባኖስ ህዝብ ለሶርያ ዜጎች ያለውን ድጋፍ አደባባይ በመውጣት ገልጾዋል። ይህ በዚህ እንዳለ የሶርያ መንግስት ጦር ኃይላት ዛሬም በወሰዱት ርምጃ በቢኒሽ ከተማ አራት ሰዎች መግደላቸውን የመብት ተሟጋቾች አስታውቀዋል።

ነቢዩ ሲራክ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ