በሶማልያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት
ሰኞ፣ መጋቢት 10 1999ማስታወቂያ
ይህን አስታኮ ህዉከት እና ግጭት እየተበራከተ በመጣበት በሶማልያ በሚገኙ የእርዳታ ድርጅት ሰራተኞች፣ ኢላማ እየሆኑ ነዉ ሲል አስጠንቅቆአል። ይህ በንዲህ እንዳለ በትናንትናዉ እለት የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ልኡካን ቡድን ባይደዋ መግባታቸዉ ታዉቋል። ልኡካኑ ከተለያዩ የአሪገቷ ባለስልጣናት፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጌዲ እንዲሁም ከሶማልያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢስማኢል ቡባ ጋር የተባበሩት መንግስታት ጦር ሰራዊት ከስድስት ወር በኳላ በሶማልያ ሊሰፍር የሚችለበት ሁኔታ ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል። Eric Laroche ን አዜብ ታደሰ በስልክ አነጋግራአቸዉ ነበር