1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሶማልያ በመባባስ ላይ ያለዉ የቦንብ ጥቃት

ሰኞ፣ ግንቦት 27 1999

በሶማልያ፣ መቅዲሾ ዉስጥ፣ በአጥፍቶ ጠፊ፣ እንዲሁም በተጠመደ ቦንብ ፍንዳታ የሚጠፋዉ የሰዉ ህይወት እየተበራከተ መምጣቱ ተገለጸ

https://p.dw.com/p/E0YK
በመቅዲሾ የፍንዳታ ጉዳተኞች
በመቅዲሾ የፍንዳታ ጉዳተኞችምስል AP

የአገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር አሊ መሃመድ ጊዲ፣ ትናንት፣ ለሶስተኛ ግዜ ከተጠነሰሰባቸዉ ጥቃት አምልጠዋል። ነገር ግን ሰባት ያህል የሚኒስትሩ ጠባቂዎቻቸዉ ተገድለዋል፣ በርካቶችም ቆስለዋል። በተያያዘ ዜና በትናንትናዉ እለት በመቅዲሾ ዉስጥ መንገድ ዳር የተጠመደ ቦንብ ያስከተለዉ ፍንዳታ፣ በኢትዮጽያ የጦር ሰራዊት ተሽከርካሪ ላይ ጉዳት አድርሶአል። ስለ ሶማልያ ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ጋዜጠኛ አዊስ ኦስማን ዩሱፍን፣ አዜብ ታደሰ በስልክ አነጋግረዋለች።