በስደት ህይወቱ ያለፈዉ ጋዜጠኛ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 5 2007ማስታወቂያ
ጋዜጠኛ ወደ ኬንያ የተሰደደዉ የኢትዮጵያ መንግሥት ያሥረኛል ወይም ይከሰኛል በሚል ፍራቻ ነበር።
ተወልዶ ያደገው የጋዜጠኝነት ሥራውንም የጀመረው በይርጋጨፌ አካባቢ ነበር። ደቡባዊ-ኢትዮጵያ። በኢትኦጵ ጋዜጣና እና ቁም ነገር መጽሄት ላይም ሠርቷል-ጋዜጠኛሚሊዮንሹሩቤ። ላለፉት ሶስት አመታት ማራኪ የተሰኘ የግል ጋዜጣ በዋና ስራ አስኪያጅነት በመምራት ላይ የነበረው ሚሊዮን ጳጉሜ 5/2006 ዓ.ም. ወደ ኬንያ ከሌሎች አራት የሙያ ባልደረቦቹ ጋር መሰደዱን ጋዜጠኛ መላኩ አማረ ይናገራል። ኬንያ ሲደርስ ጋዜጠኛ ሚሊዮን ጤነኛ ነበር የሚለው መላኩ ባለፉት 12 ቀናት ግን የጤና ሁኔታው በማሽቆልቆሉ ተደጋጋሚ ህክምና ለማግኘት ሞክሮ ነበር።ሚሊዮን ለሞት የተዳረገበት ምክንያት እስካሁን በግልጽ አልታወቀም። መላኩና በኬንያ የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች አስከሬኑን በኢትዮጵያ በክብር ለማሳረፍ ሙከራ በማድረግ ላይ ናቸው። ጋዜጠኛ ሚሊዮን የአንዲት ታዳጊ ወጣት አባት ነበር።
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ