1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በስኬትቦርድ ከአዲስ አበባ እስከሐረር ጉዞ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 18 2005

ካሳለፍነው ማክሰኞ ጀምረው ሰባት ኢትዮጵያዊ እና የውጭ ዜግነት ያላቸው ወጣቶች ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ ሀረር ጎዞ ጀምረዋል። ጉዞዋቸው በመኪና ወይንም በብስክሌት አይደለም፤ በስኬትቦርድ ነው።

https://p.dw.com/p/18NPh

ትንሽ ነው ከጠፍጣፋ እንጨት የተሰራ፣አራት ጎማዎች ያሉት ምናክባትም መካከለኛ መክተፊያ ያልላል። ሰሞኑን ፤አዲስ አበባን ከሀረር ከሚያገናኘው ጎዳና ላይ እንደዚህ አይነት እንጨት ላይ ቆመው ወይንም በአንድ እግራቸው እየገፉና ጣውላው ላይ ዘለው እየቆሙ የሚጓዙ ወጣቶች አይታችሁ ከሆነ ፤ የስኬትቦርድ ነጂዎች ናቸው። ስለዚህ ረዥም ጉዞ እና የስኬት ቦርድ አነዳድ የዛሬው የወጣቶች አለም ትኩረት ይሆናል።

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ