1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በስሕተት ተያዘው የተባለው ኤርትራዊ ማንነት ጉዳይ

Merga Yonas Bulaሐሙስ፣ ሰኔ 2 2008

በትላንትናዉ እለት የጣልያን እና የታላቋ ብርታንያ መንግስት ስድተኞችን በህገ ወጥ መንገድ በማዘዋወር ስራ ላይ ተሰማርተዋል ብለው ሲያድኑት የቆዩትን ኤርትራዊዉን መርዕድ ይህደጎ መድሃኔ ፣ ወይም በቅፅል ስሙ «ዘ ጄኔራል፣ በመባል የሚታወቀዉ በቁጥጥር ስር አዉለናል ስሉ መግለጫ ሰጥተዋል።

https://p.dw.com/p/1J3v5
Flüchtlinge in Rom
ምስል D. Cupolo

[No title]

የ35 ዓመቱ መርዕድ በጎርጎረሳዊያኑ 2013 ዓ/ም 359 ሰዎች ሜድትርያንያን ባህር ሲያቋርጡ ለሞቱት ተጠያቂና እና ስደተኞችንም በማሰቃየት የሚታወቅ ነበር። ይሁን እንጅ በሱዳን ካርቱም ተያዘ የተባለዉ ግለሰብ ፣ መርዕድ ይህደጎ መድሃኔ አለመሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ለዶቼቬለ አስረድተዋል። እነርሱ እንደሚሉት ትናንት የተያዘው መርዕድ ይህደጎ መድሃኔ ሳይሆን መርዕድ ተሰፈማርያም መሆኑን ቤቴሰቦቹና ዘመዶቹ ይናገራሉ። ስዊድን የሚኖሩት ትውልደ ኤርትራዊቷ የመብት ተሟጋች ሜሮን እስጢፋኖስ ይህንኑ ለዶቼቬለ ገልፀዋል።


<<መጀመሪያ ጥዋት ሰበር ዜናዉን የተናገረዉ ቢቢሲ ነበር። የጣሊያን መገናኛ ብዙሃንም ዘግበውበታል ።በዚህም ዘገባ ሰዎችን በማዛወር የሚጠረጠረው ግለሰብ ትክክለኛ ፎቶግራፍ ነበራቸዉ። ይህም በጣም ገርሞኝ ቀኑን ሙሉ ስከታተል ቆየሁ። ግን በኋላ ላይ የጣልያን ምድያዎችንያሰሩትን ግለሰብ ፎቶግራፍ አሳተሙት። ባተሙት ፎቶግራፍም በግልፅ ሙሉ በሙሉ ሁለት የተለያዩ ግለሰቦች ናቸዉ። ከዛም በኋላ የታሰርዉ ኢህት፣ የአጎት ልጅ፣ ጓደኞቹ፣ የትምህርት ጓደኞቹ፣ አብሮት የምኖሩ እና ሁሉም አግኝተውኝ ትክክለኛ ሰዉ እንዳልሆነ ነገሩኝ። ከዛም በኋላ ጉዳዩን ለማጠራት መርዕድ ይህደጎ መድሃኔ ታግዘው የመጡ ስድተኞች ደወለኩላቸዉ እና ጣልያኖች ያተሙት ፎቶግራፍ አሳየዋቸዉ፣ ከዛም ሁሉም አይ ይሄ እሱ አይደለም አሉኝ። ከዛም በዋላ የተሳሳተ ግለሰብ እንደያዙ እርግጠኛ ሆንኩ።>>


ተፈላጊው መርዕድ ይህደጎ መድሃኔ ከዚህ በፊት በሱዳን መንግስት ቁጥጥር ስር ቢዉልም ጉቦ በመስጠት ከእስር ቤት መዉጣቱን ሱዳን የሚገኙ ሰዎች እንደሚናገሩ ሜሮን ለዶቼቬለ ገልፃለች ። ካርቱም የምትኖረዉ እና በስህተት ኢጣልያ ተወስዷል የተባለው የመርዕድ ተሰፈማርያም እህት ሰገን ተስፈማርያም ታናሽ ወንድሟ 29 ዓመቱ መሆኑን ተናግራ ከሁለት ሳምንት በፊት ስድስት የሱዳን ፖሊሶች ከነበረበት ከአፍሪቃ ኮርኔር ካፌ እንደያዙት ትናገራለች። ከዛ በኋላ የተፈፀመዉን ስታስረዳም፣ <<ከዛ በዋላ ወደ ቤቱ ይዘውት ሄዱ፣ ቤቱን በረበሩት፣ ምንም አለገኙም እና እሱ እንዲናገር ግዜም አልሰጡትም። እሱ አረብኛም ሆነ እንግልዘኛ አይናገርም። ይዞት ከሄዱ ከሁለት ሳምንት በኋላም የት እንዳለ አላወቅኩም፣ ከዛም እሱም ለማግኘት ካርቱም ያሉ ሁሉም እስርቤቶች ሳስሰዉ ነበር። ግን እነሱም በዚህ ስም ማንም እንደማያዉቁት ነገሩኝ። የሱዳን ፖሊሶች ባይነግሩኝም ትላንት በእንቴርኔት ላይ እሱ ወደ ጣልያን ተይዞ እንደተወሰደ አነበብኩ። እኔም ደነገጥኩኝ።>>

Eritrea Flüchtlingslager in der Region Tigrai Äthiopien
ምስል Reuters/T. Negeri


ከመርዕድ ተሰፈማርያም ጋር የስጋ ዝምድና ባይኖረንም አብሮ አደገ ነን የሚለዉ በጣልያን የፓሌርሞ ነዋሪ የሆነዉ ፍሳሃዬ ትስፋይ ዜናዉን ሲሰማ መደንገጡን ተናገራል። እሱን ለማስፈታት እየተደረገ ያለዉን ጥረትእየተደረገ መሆኑን ተናግሯል። ወንድሜ የስድተኛ አዘዋዋሪ አይደልም የምትለዉ እህቱ ሰገን ወንድሟን ለማስፈታት ጥረት እያደረገች መሆኑን ተናግራ የጣልያን መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድም አሳስባለች።

መርጋ ዮናስ

ሒሩት መለሰ