በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሮሮ 6 ግንቦት 2007ሐሙስ፣ ግንቦት 6 2007ሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፓስፖርታቸውን ለማሳደስ ወይም በሌላ ለመቀየር ረጅም ጊዜ በመውሰዱ መቸገራቸውን ገለጹ። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ሳዑዲ አረቢያ በተለይም ጂዳ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ቆስላ አሮጌ ፓስፖርታቸዉን ሰብስቦ አዲሱን ግን ለረጅም ጊዜ አልሰጣቸዉም።https://p.dw.com/p/1FPqmምስል imago/Paul von Stroheimማስታወቂያ በዚሕም ምክንያት የመኖሪያ ፍቃዳቸዉ ጊዜ ማለፉን ወይም ሊያልፍ መቃረቡን ይናገራሉ። እንደሚሉትም ፓስፖርታቸውን እንዲታደስ ወይም እንዲቀየር ሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የጠየቃቸውን ገንዘብ ቢከፍሉም፤ የታደሰዉን ፓስፖርት ለማግኘት ከአምስት ወራት በላይ ጠብቀዋል። እስካሁን አላገኙትም። እሸቴ በቀለ ነጋሽ መሐመድ