1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በምዕራቡ አለም የገና በአል አከባበር

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 16 2002

በዛሪዉ እለት በአለም ዙርያ የጎርጎረሳዉያኑን የቀን ቀመር የሚከተሉ ካቶሊኮች እና ወንጌላዉያን የገና በአልን በማክበር ላይ ይገኛሉ። በጀርመኖች ዘንድ ተወዳጅ የሆነዉን የገና በአልን በማስመልከት ዛሪ ልዩ ዝግጅት ይዘናል።

https://p.dw.com/p/LDZ6
በኮለኝ ከተማ የገና አከባበርምስል picture-alliance/Bildagentur H

የካቶሊካዉያኑ የሃይማኖት አባት በቡራኪያቸዉ ለአለም ሰላም እና እና ህብረት ጥሪ ያቀረቡበት እና የጣልያንን የገና በአል አከባበር ስርአት እናያለን፤ ከዝያም ለጀርመናዉያን የገና በአልን ማክበር ዝግጅት፣ ደስታ ወይስ ጭንቀት በሚል ርእስ፣ ከበርሊን የደረሰን ዘገባ በጀርመናዉያኑየገና አከባበር ዙርያ ሲያቆየን፣ የአከባበሩ ስነ-ስርአት ስጦታ መሰጣጣቱ በክርስትናዉ ሃይማኖት ዘንድ ብቻ ወይስ እንዴት በሚል ከእንግሊዝ የደረሰን ዘገባ በዚህና የእንግሊዛዉያንን የገና በአል አከባበር ያስቃኘናል፣ የገና ዛፍን በማሸብረቅ፣ የበረዶ ክምሩ፣ በአሜሪካ የተለመደ ቢሆንም በተለይ በመጠናቀቅ ላይ ባለዉ የአዉሮጻዉያኑ 2009 አ.ም የኢኮነሚ ቀዉስ የጎነጣት አሜሪካ የገና በአልን እንዴት በማክበር ላይ ናት መልስ ያዘለ ዘገባ ከዝያዉ ከዋሽንግታን ደርሶናል። በመጨረሻም በጀርመን ወጣቱ በገና በአል ደስታን ወይንስ ድብርትን ያተርፋል፣ ጀርመናዉያን ወጣቶች የገና በአልን እንዴት ይቀበሉታል፣ እዚህ ላይ ኢትዮጽያዉያን ወጣቶችም መልስ አላቸዉ፣ በቦን ዙርያ መቅረጽ ድምጻችንን ከፍተን አዳምጠን ይዘናል። ያድምጡ

አዜብ ታደሰ፣

ተክሌ የኋላ