በምሥራቅ የዩክሬይን ከተማ በስሎቭያንስክ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሩ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 24 2006ማስታወቂያ
ምሥራቁ ዩክሬይን እንዲገነጠል የሚሹት ወገኖች በተጠቀሰችው ከተማ 2 ሄሊኮፕተሮች መትተው መጣላቸውንና ሁለቱም አብራሪዎች መሞታቸውን የዩክሬይን መከላከያ ሚንስቴር አስታውቋል።
የኪየቭ መንግሥት ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች ወደ ስሎቫንስክ በማምራት ላይ መሆናቸውንና ወደ ከተማይቱ ሠርገው የገቡ ወታደሮች እንዳሉ፤ በተለያዩ ጣቢያዎችም ውጊያ መከፈቱን ፤ ቭላዲስላቭ በሚል የመጀመሪያ ስም የሚጠቀሱት የመፍቀሬ ሩሲያውያኑ ወታደራዊ ክንፍ ይፋ ቃል አቀባይ አስታወቀዋል።
ተክሌ የኋላ