1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በመኖሪያ ቤት ውስጥ መማር (Homeschooling)

ረቡዕ፣ ግንቦት 26 2001

አዳጊ አገሮች በኤኮኖሚ ችግርና በተለያዩ ልማዳዊ መሰናክሎች፣ ልጆቻቸውን ወደ መደበኛ ዘመናዊ ት ቤቶች ለመላክ ሲቸገሩ በኢንዱስትሪ እጅግ በገሠገሡት ሃገራት በተለይ በዩናይትድ ስቴትስ፣

https://p.dw.com/p/I2w8
ምስል AP

ለዬት ያለ ትምህርት ቤት እየተስፋፋ በመሄድ ላይ መሆኑ ይነገራል። እርሱም፣ በመኖሪያ ቤት ውስጥ መማር (homeschooling) የተሰኘው ነው። ይህ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ፣ ማለትም ወላጆች ባመዛኙ እናቶች ልጆቻቸውን የሚያስተምሩበት ፈሊጥ፣ ተቀባይነት እያገኘ የመሄዱን ያህል ነቀፌታም አላጣውም።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ 1.5 ሚልዮን ልጆችና ለጋ ወጣቶች፣ መደበኛ ትምህርት የሚከታተሉትም ሆነ የሚቀስሙት ፣ ወደ መንግሥትም ሆነ የግል ትምህርት ቤት በመጓዝ ሳይሆን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ነው። «ሆም እስኪሊንግ » ከሞላ ጎደል በመላዋ ዩናይትድ ስቴትስ ህጋዊ ዕውቅና ቢያገኝም፣ በዚህ ዓይነቱ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ላይ ቅሬታ የሚያሰሙና ነቀፌታ የሚሠነዝሩ ወገኖች አልታጡም።

ተክሌ የኋላ፣አርያም ተክሌ