1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሐገር ጎቢኚዎች ላይ የደረሰዉ አደጋ: ኢትዮጵያና ኤርትራ

ሐሙስ፣ ጥር 10 2004

ኢትዮጵያ ራስዋን የመከላከል መብት አላት በማለትም አስጠንቅቋል።---የኤርትራ መንግሥትም ከኢትጵያ የሚሠነዘርበትን ወቀሳና ዉግዘት በተደጋጋሚ ዉድቅ አድርጎቷል

https://p.dw.com/p/13mo4
በሕይወት ከተረፉት ጎብኚዎች ጥቂቱምስል AP

19 01 12

በሐገር ጎቢኚዎች ላይ የደረሰዉ አደጋ: ኢትዮጵ

የኢትዮጵያ መንግሥት ፥አዉሮጳዉያኑን ሐገር ጎብኚዎች የገደሉ፥ ያቆሰሉና ያገቱት ሐይላት በኤርትራ መንግሥት የሠለጠኑና የታጠቁ ናቸዉ በሚለዉ አቋሙ እንደፀና ነዉ።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንንስቴር ትናንት ማምሻዉን ባወጣዉ መግለጫ ለአጋዉ ተጠያቂ ያደረገዉን የኤርትራን መንግሥት አለም አቀፉ ማሕበረሰብ እንዲያወግዘዉ ጠይቋል።መግለጫዉ ኢትዮጵያ ራስዋን የመከላከል መብት አላት በማለትም አስጠንቅቋል።የኢትዮጵያ መንግሥትን አቋም በተመለከተ ነጋሽ መሐመድ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን በሥልክ አነጋግሯቸዋል።

--------------------------------------------------------------------------------------------------
በሐገር ጎቢኚዎች ላይ የደረሰዉ አደጋና ኤርትራ

የኤርትራ መንግሥትም ከኢትጵያ የሚሠነዘርበትን ወቀሳና ዉግዘት በተደጋጋሚ ዉድቅ አድርጎቷል ። የኤርትራ ማስተዋቂያ ሚንስትር አቶ ዓሊ አብዶ ዛሬ እንዳስታወቁት መንግሥታቸዉ እንዲሕ አይነቱን አደጋ ፈፅሞ አያደርስም፥ አደጋዉን አደረሱ የሚባሉትን ወገኖች አይረዳምም።እንዲያዉም ሚንስትር ዓሊ አብዶ እንደሚሉት አዉሮጳዉያኑን ሐገር ጎብኚዎች የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ራሳቸዉ ሳይስገድሉ፥ ወይም ሳያሳግቷቸዉ አልቀሩም።አቶ ዓሊ አብዶን ነጋሽ መሐመድ በስልክ አነጋግሯቸዋል።

«የሕዋሐትን (የኢትዮጵያ አላልኩም ምክንያቱም ኢትዮጵያ የተከበረች ሐገር ናት) ባለሥልጣናትን ያለፈ ታሪክ ባሕሪ ሥንመለከት፥ ይሕ በሕወሐት ሥርዓት ተፈፅሟል የሚለዉን ከግምት አላወጣዉም።ምክያቱን በዊኪሊክስ እንደተጠቀሰዉ ከዚሕ በፊትም (የሕወሐት ባለሥልጣናት እንዲሕ አይነት የሽብር ምግባር ርዕሠ ከተማ አዲስ አበባ ዉስጥ ፈፅመዋልና።ሥለዚሕ ይሕ በሕወሐት ሥርዓት ተፈፅሟል የሚለዉን ከግምት አላወጣዉም።»

ምን መረጃ ይዘዉ ነዉ-ይሕን የሚሉት።የኢትዮጵያ መንግሥት ወይም እርስዎ እንዳሉት የሕወሐት መንግሥት ይሕን አደጋ የሚያደርሰዉ ምን አልሞ፥ ምን ለመጠቀም ነዉ።

«ሥርዓቱ የኢትዮጵያን ሕዝብ በማግለል ጠባብ መርሆቹ ምክንያት የዉጪ ሐይላት መሣሪያ ሆኗል።አብሮም ደግሞ (ሥርዓቱ) ኢትዮጵያን ወደ የአካባቢዉ አለመረጋጋት ለዉጧታል። እንደሚታወሰዉ በ2006 (እንደ ጎ.አ.) ኤርትራ ሁለት ሺሕ ወታደሮች አዝምታለች ብሎ አዉግዟት ነበር።ይሕን ዉሽትነቱ ተጋልጧል።በሁለት ሺሕ ሁለትም ባድሜ ለኔ ተፈርዳልኛለች በማለት ለኢትዮጵያ ሕዝብ በጠራራ ፀሐይ ዋሽቶ ነበር።እንዲሕ ዓይነቱ ሁኔታ የሕወሐት ሥርዓት የተለመደ ባሕሪ ነዉ።

ባለፈዉ ዓመት ልክ በዚሕ ጊዜ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ ሲካሔድ-ኤርትራ አዲስ አበባን በቦምብ ለመምታት አሲራለች በማለት ወቅሶ ነበር።ይሕም ዉሸትነቱ ተጋልጧል።አሁንም ይሕንን ጊዜ የመረጠዉ ሆን ብሎ ለፖለቲካ ዉስልትና ነዉ።»

Äthiopien Vulkan Erta Ale Afar Region
ምስል picture-alliance/dpa

-በድንበሩ በሁለቱም በኩል የታጠቁ ሐይላት እንደሚንቀሳቀሱ ይታወቃል።ለምሳሌ አርዱፍ።አደጋዉን ከእነዚሕ ሐይላት አንዳቸዉ አላደረሱትም ብለዉ በትክክል ያምናሉ።---

«ኤርትራዉያን እንዲሕ አይነቱን ቁሻሻ ምግባር አሁንም ሆነ ድሮ -በትግሉ ወቅት፥ ሊፈፅሙት ቀርቶ አስበዉትም አያዉቅም።----አደጋዉን ያደረሰዉ ወገን ማንም ሆኖ ማን ትርጉም የለሽ ነዉ።ጨርሶ ትርጉመ ቢስ ነዉ።ኢሠብአዊ (ድርጊት) ነዉ።»
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ














Vulkan Erta Ale in Äthiopien
ምስል picture alliance/Lonely Planet Images