1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሊቢያ አቀባበል የብሪታኒያ ቁጣ

ዓርብ፣ ነሐሴ 15 2001

ከሀያ አንድ ዓመት በፊት ሎከርቢ ሰማይ ላይ በፈነዳው የፓን አሜሪካን አውሮፕላን ለጠፋው የሰው ህይወትና ንብረት በጥፋተኝነት ተወንጅሎ የዕድሜ ልክ እዕስራት የተፈረደበት ሊቢያዊው አቤል ቤሴት አል ሜግራሂ ትናንት ተለቆ ወደ ሀገሩ ሲገባ የተደረገለት የጀግና አቀባበል ተደረገለት።

https://p.dw.com/p/JG0m
ትሪፖሊ አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርስምስል AP

ይህ አቀባበል የብሪታኒያን መንግስትና አሜሪካንን አስቆጥቷል። የብሪታኒያ ውጭ ጉዳዪ ሚኒስትር ዴቪድ ሚሊባንድ አቀባበሉን በጣም የሚያበሳጭ ብለውታል ። አቤሌ ቤሴት ትናንት ትሪፖሊ ሲገባ በርካታ ህዝብ የተቀበለው ሲሆን ከአውሮፕላኑ በሚወርድበት ጊዜም አንዳንዶች አባባ በመበተን ነበር የተቀበሉት ። ሀና ደምሴ ዝርዝር አላት

ሀና ደምሴ ፣ ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ