በለንደን በድርቅ ለተጎዱ የእርዳታ ስብስብ
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 18 2008ማስታወቂያ
እኛዉ ለኛዉ በተሰኘዉ በዚህ ዝግጅትም እስከአምስት ሺህ የእንግሊዝ ፓዉንድ ሳይሰበሰብ እንዳልቀረ የዝግጅቱ አስተባባሪ ኮሚቴ ፀሐፊ እና የገንዘብ ማሰባሰቢያዉን መድረክ የመሩት አቶ ወንድወሰን አበበ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። የኪነጥበብ ባለሙያዎቹ በድርቅ የተጎዱት ገበሬዎች የእርዳታ ስንዴ ከመጠበቅ ይልቅ ዉኃን አዉጥተዉ ለእርሻቸዉ የሚያዉሉበት መሣሪያ ወይም ቴክኒዎሎጂ እንደሚሹ በመረዳታቸዉም አቅማቸዉ በፈቀደ የዉኃ ማዉጫ ማሽን ገዝተዉ በድርቁ ክፉኛ ለተጎዱ አካባቢዎች እንኳ ለመስጠት ማሰባቸዉንም አስረድተዋል። የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ኮሚቴዉን ፀሐፊ ሸዋዬ ለገሠ በአጭሩ ስለዝግጅቱ ጠይቃቸዋለች።
ሸዋዬ ለገሠ
እሸቴ በቀለ