1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በህገ ወጥ መንገድ ከኢትዮጵያ የሚወጣ ገንዘብና ተፅዕኖው

ሐሙስ፣ ኅዳር 28 2004

እ.ጎ.አ በ 2009 ብቻ ከኢትዮጵያ በህገ ወጥ መንገድ የወጣው ገንዘብ ወደ 3.26 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ አንድ ዓለም ዓቀፍ ተቋም አስታወቀ ።

https://p.dw.com/p/S0p0
ምስል ullstein bild - CARO/Hoffmann

ግሎባል ፋይናንሻል ኢንግሪቲ የተባለው ድርጅት ባወጣው ዘገባ እንዳስታወቀው ገንዘቡ ከዚያ በቀደሙት 2 ዓመታት ከሃገሪቱ በህገ ወጥ መንገድ ከወጣው ገንዘብ በእጥፍ ይበልጣል ። ተቋሙ ባወጣው ጥናታዊ ፅሁፍ ይኽው ገንዘብ በሙስና በጥቅማ ጥቅምና በስርቆት ከሃገር እንደሸሸ ጠቁሟል ። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል ።

አበበ ፈለቀ

ሂሩት መለሰ