1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ቅድሚያ ለሴቶች» የ 5 ኪሎ ሜትሩ ሩጫ

ዓርብ፣ መጋቢት 11 2007

ባለፈው እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ ቁጥራቸው በሺ የሚቆጠሩ ሴቶች ሮጠዋል። ከነዚህም ውስጥ 700 የሚሆኑት የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ናቸው። የሴቶችን ተሳትፎ እና መብት ለማበረታታት በየዓመቱ ስለሚካሄደው የሩጫ ውድድር በዛሬው የወጣቶች ዓለም እንመለከታለን።

https://p.dw.com/p/1Eu4w
Addis Abeba Women grace 2015
ምስል A. Gudeta

ትላልቅ የሩጫ ውድድሮች በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ከጀመሩ ዓመታት ተቆጠሩ። ከነዚህ የሩጫ ውድድሮች መካከል ባለፈው እሁድ የተካሄደው «ቅድሚያ ለሴቶች» የ 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ አንዱ ነው። ይህ ውድድር የተዘጋጀው በታላቁሩጫበኢትዮጵያኃላፊነቱየተወሰነየግልማህበርነው። ከታዋቂው እና ባለፈው ህዳር ለ 14ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ከተካሄደው «ታላቁሩጫ» በተጨማሪ ሌላ፤ ሴቶች ብቻ የሚሳተፉበት ሩጫ ማዘጋጀት ለምን አስፈለገ? የዚህ ውድድር አዘጋጅ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ኤርሚያስ አየለን ጠይቀናል።

በዚህ የሩጫ ውድድር ከተሳተፉት ሴቶች አንዷ፤ ባለፈው ዓመት ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በህግ የተመረቀችው ህሊና ብርሃኑ ናት። ህሊና፤ ሴቶች ብቻ በሚወዳደሩበት ሩጫ ስትሳተፍ ይህ 4ኛ ጊዜዋ ነው። ለወጣቷ ሩጫው ከስፖርት የበለጠ ትልቅ አላማ አለው፤ስለዚህ አላማ ወጣቷ ገልጻልናለች።

Addis Abeba Women grace 2015
የሽልማት ስነ ስርዓትምስል A. Gudeta

በዶይቸ ቬለ የፌስ ቡክ ገጽ ላይ ያለ ዕድሜ ጋብቻ በመፈፀም እና በተለያዩ ምክንያቶች ልጃ ገረዶች ወደ ትምህርት ቤት የማይላኩበት ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ጠይቀን ነበር። ከደረሱን አስተያየቶች ጥቂቶቹ፤

ስለ የ«ቅድሚያ ለሴቶች» የ 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር እና አላማ የበለጠ ከወጣቶች ዓለም ዝግጅት የድምፅ ዘገባ ያገኛሉ። ከዚህ በታች ይጫኑ

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ