ቃለ-ምልልስ ከአትሌት ፈይሳ ሌሊሳጋር
ዓርብ፣ ነሐሴ 20 2008ማስታወቂያ
በርዮው ኦሎምፒክ በማራቶን የብር ሜዳልያ ካሸነፈ በኋላ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ተቃውሞውን በመግለጽ ወደ ሃገሩ ሳይመለስ የቀረው አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ ኢትዮጵያውያን አድናቆታቸውን እየገለጹለት መሆኑን አስታወቀ ። ፈይሳ ለዶቼቬለ በሰጠው ቃለ ምልልስ ባደረገው እና በውሳኔው እንደሚኮራ ተናግሯል ። በውድድሩ ማብቂያ ላይ እጁን ወደ ላይ አውጥቶ በማጣመር በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ያለውን ተቃውሞ የገለጸው ፈይሳ ይህን በማድረጉ የመገደል ወይም የመታሰር ስጋት ስላለው ወደ ሃገሩ እንደማይመለስ በተወዳደረበት ዕለት በሰጠው መግለጫ ላይ ተናግሮ ነበር ።የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ፈይሳ በርዮ ባሳየው ተቃውሞ ምክንያት እንደማይቀጣ ነበር ያስታወቀው ። አትሌት ፈይሳን የለንደንዋ ዘጋቢያችን ሃና ደምሴ አነጋግራዋለች ።
ሃና ደምሴ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ