1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቀጣዩ አጠቃላይ ምርጫና የፓርቲዎች ተሳትፎ ጉዳይ

ረቡዕ፣ መጋቢት 2 2001

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እንዳስታወቀው፡ ተሻሽሎ በወጣው የምርጫ ህግ መሰረት፡ በሁለት ተከታታይ ምርጫዎች ያልተሳተፉ ፓርቲዎች በቀጣዩ የ 2002 ዓም አጠቃላይ ምርጫ በተወዳዳሪነት እንዳይቀርቡ ሊታገዱ ይችላሉ።

https://p.dw.com/p/HA07
ምስል AP GraphicsBank/DW

ቦርዱ ባለፉት ሁለት ምርጫዎች አልተሳተፉም ያላቸውን ፓርቲዎች ስም ዝርዝር አውጥቶ በህግ ሊወሰድ የሚገባውን ውሳኔ እንዲያሳልፍ ዝርዝሩን ለቦርዱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ማቅረቡን ገልጾዋል። ይህ በሁለት ተከታታይ ምርጫዎች ያልተሳተፉ ፓርቲዎች ከቀጣዩ አጠቃላይ ምርጫ ተሳትፎ ሊታገዱ ይችላሉ የተባለበት ዜና ከያቅጣጫው የተለያየ አስተያየትና ተቃውሞ አስነስቶዋል። ይሁንና፡ በሁለት ተከታታይ ምርጫ ሲባል በሁለት አጠቃላይ ወይም በሁለት የማሟያ፡ ወይም በሁለት አጣቃላይና የማማያ ምርጫ መሆኑ በህጉ በግልጽ ያልተጠቀሰበት ጉዳይ ህጉን አሻሚ እንዳደረገው የህግ ባለሙያው አቶ ገብረጻዲቅ ተመስገን በተለይ ለዶይቸ ቬለ አስታውቀዋል። ታደሰ እንግዳው

AA/NM