1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቀኝ አክራሪነት በጀርመን

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 24 2004

በአንዳንድ ስፍራዎችም የውጭ ዜጎች ወደ ሃገራቸው የሚመለሱበትን ጊዜ እንዲያሳውቁ የሚገልጹ ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ እየደረሱዋቸው ነው ። ይህን መሰሉ እርምጃና ጫና የቀኝ አክራሪዎችን እንቅስቃሴዎች በይፋ በሚቃወሙት ላይም ይበልጡን ተጠናክሯል

https://p.dw.com/p/14nfV
ARCHIV - Teilnehmer an einer rechtsextremen Kundgebung stehen am 04.09.2010 in Dortmund auf einem Parkplatz neben einem Polizeibeamten. Die Polizei ist am Dienstag (07.09.2010)in neun Bundesländern gegen gegen die neonazistische «Hilfsorganisation für nationale politische Gefangene und deren Angehörige e.V.» (HNG) vorgegangen. Dabei wurden nach Angaben des Bundesinnenministeriums in Berlin rund 30 Wohnungen von Funktionären, Mitgliedern und Anhängern durchsucht und Unterlagen beschlagnahmt. Foto: Rene Tillmann dpa/lnw (zu dpa 4108 vom 07.09.2010) +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture alliance / dpa

ከምስራቅና ምእራብ ጀርመን ውህደት በኋላ የውጭ ዜጎች ላያ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን የሚፈፅሙት ቀኝ አክራሪዎች በምሥራቅ ጀርመን ብቻ እንደተወሰኑ ተደርጎ ነበር የሚገመተው ይሁንና አሁን በምዕራባዊው የጀርመን ክፍልም የአፍቃሪ ናዚዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ።

በምሥራቅ ጀርመን እንቅስቃሴያቸው ተጋኖ ይነገር የነበረው ቀኝ አክራሪዎች አሁን እንደሚታሰበው እንዳይደለ የቮልፍጋንግ ዲክ ዘገባ ያስረዳል ። በምሥራቁም ሆነ በምዕራብ ጀርመን በቀኝ አክራሪዎች የሚፈፀሙት ወንጀሎች ቁጥር አሁን መሳ ለመሳ ሆኗል ። በተለይ በሰሜናዊቷ ከተማ በሃምቡርግ በምእራባዊቷ በዶርተሙንድና በደቡባዊቷ በኑርምበርግ በቀኝ አክራሪዎች የተጠናከሩ ጥቃቶች እየተካሄዱ ነው ። በነዚህን መሰል ከተሞች የውጭ ዜጎችን በየጎዳናው የሚያሸማቅቁ ድርጊቶች ይፈፀማሉ ፤ ማስፈራሪያዎች ይደርሱዋቸዋል ። በስለት ይወጋሉ ፤ መቃብሮች ሳይቀሩ የጥቃት ዒላማ ውስጥ ገበተዋል ። የናዚዎች ምልክቶች በየግድግዳው ይለጠፋል ።

Neonazis demonstrieren
ምስል AP

በአንዳንድ ስፍራዎችም የውጭ ዜጎች ወደ ሃገራቸው የሚመለሱበትን ጊዜ እንዲያሳውቁ የሚገልጹ ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ እየደረሱዋቸው ነው ። ይህን መሰሉ እርምጃና ጫና የቀኝ አክራሪዎችን እንቅስቃሴዎች በይፋ በሚቃወሙት ላይም ይበልጡን ተጠናክሯል ። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ካሉት መካከል ሚሻኤል ሄልምብሬሽት ይገኙበታል ። ሄልምብሬሽት ቀኝ አክራሪዎችን በመቃወም የተመሠረተ ድርጅት መሪ ናቸው ። እርሳቸውና ቤተሰባቸው ለ3 ቀናት ከ2 መቶ በላይ በሚሆኑ ቀኝ አክራሪዎች ተከበው ነበር ። አሁን ቤታቸው በፖሊስ ይጠበቃል ። ሄልምብሬሽት ለቀናት ከተካሄደባቸው ከበባ በኋላ የኃይል እርምጃ ለመውሰድ በተዘጋጁ ሰዎች በቤታቸውና በመኪናቸው ላይ ጥቃት ደርሷል ።

« መኪናው መሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኗል ፤ መስታወቶቹን ሰባብረው፤ ጎማዎቹን በስለት አስተንፍሰዋል ፤ በቤታችን ላይም መጥፎ ሽታ ያለው አደገኛ አሲድ በመርጨታቸውና ይህም ለአንድ ሳምንት ያህል ሲያቅለሸልሸን ነወ የከረመው ። እጅግ አደገኛ ጥቃት ነበር ። »

Springerstiefel
ምስል AP

አፍቃሪ ናዚዎች እንደቀድሞው በድብቅ መንቀሳቀሳቸውን ቀንሰዋል ። ብዙም ድምጹ የማይሰማ ደጋፊ አለን በለው ያምናሉ ። በደቡባዊው የባቫርያ ፈደራዊ ክፍለሃገር ውስጥ በሚገኘው በግሬፍንበርግ በ3 ዓመታት ውስጥ ከ50 ለሚበልጥ ጊዜ ሰልፍ ወጥተዋል ። ሁሌም ጊዜም ግን ሰልፉ አምባጓሮ እንደሚያስነሳ ሚሻኤል ሄልምብሬሽት ያስረዳሉ ።

« በዚህ አካባቢ እንደምንታዘበው ወሳኝና ስር ነቀል ለውጥ የሚታይበት እንደሚሆን ነው ። እንደሚሰማኝ በዚህ በባቫርያ የሚካሄደው እንቅስቃሴውን የሚቃወም ይህን መሰል የጀግንነት ተግባር ምን ጊዜም የሚታወስበት ሁኔታ ይኖራል ። »

ፖሊስ ና የህገ ምንግሥቱ አስከባሪዎችን የመሳሰሉ የፀጥታ ባለሥል እንደሚሉት በኑርንበርግ ብቻ 300 የኃይል እርምጃ ከመውሰድ ወደ ኋላ የማይሉ አደገኛ ቀኝ ቀክራሪዎች መኖራቸውን ማንታቸውንና ተግባራቸውን ለማውቀ የተጠናከረ ጥረት ቢደረግም የኃይል እርምጃ የሚወስዱት ሰዎች እስከዚህም ወደ ፍርድብት ቀርበው አያውቁም ። ብዙዎች ጎረቤቶች አሁን በመሃሉ አይተው እንዳላዩ ሁኔታውን ማለፍ ነው የፈለጉት ። ሰለባዎቹ ከፍርሃት ሳይላቀቁ መኖር ነው እጣ ፈንታቸው ።

NPD-Aufmarsch in Halberstadt
ምስል AP

« አዎ ሰዉ ይፈራል ። የቀኝ አክራሪነት ጠንካራ መሣሪያ ደግሞ ፍርሃት ነው ። ፍርሃቱም በአጠቃላይ ዒላማ ውስጥ በገባነው ላይ እየሰራ ነው ። »

ሁኔታውን አጥበቀው የሚተቹ ጋዜጠኞችም ታድነው ይዘመትባቸዋል ። ኽርበርት ፍዩር ኑርበርገር ናህሪሽተን ለተባለው ጋዜጣ ስለ የአፍቃሪ ናዚዎች እንቅስቃሴ ተከታታይ ዘገባዎች ያቀርባል ። በመሆኑም በቀኝ አክራሪዎች መታደን እጣው ምሆኑን ተናግሯል ።

« የሚፈፀሙትን ድርጊቶች በተመለከተ በይፋ አቋም መውሰድ ከጀመርኩበት ጊዜ አንስቶ ፍራየን ንትዘስ ሱዙድ በተባለው በቀኝ አክራሪዎች ጋዜጣ ፎቶግራፌ እየተለጠፈ እንድጠላ ይህ ንይደረግብኛል ። ይህን በቀጥታ ያልተገነዘበ ቢኖር በቀጥታ ማገናዘብ ይችላል ። »

NPD Demonstration in Oldenburg
ምስል AP

ከምሥራቅ ወደ ምእራብ ጀርመን የሄዱ በርካታ የውጭ ዜጎች አሁን በሚኖሩባቸው አንዳንድ አካባቢዎች የደህንነት ዋስትና አይ ሰማቸውም ። በኑርንበርግ ቫይስንበርገር የሚኖረው ቱርካዊው ባለግሮሰሪ ሙራት በአፍቃሪ ናዚዎች የሚደርሰበትን ጫና እንደ 3 ተኛ ደረጃ ዜጋ የመታየት ያህል ነው የሚሰማው ።

« ይህን መሰሉ ሁኔታ እንደ ውጭ ዜጋ እንደ ቱርካዊ ጀርመናዊ ሲደርስብህ ጥሩ አይደለም ። ምክንያቱም እዚህ ነው የምኖረው ።የተወለድኩት እዚህ ነው ቫይስንበርገርራዊ ነኝ ።አንዲት ሴት ልጅ አለችኝ ። በጡሩ ስሜት እዚህ ነው መኖር የምፈልገው ። »

ሙራት በሚኖርበት ከተማ የሚካሄዱትን የአፍቃሪ ናዚዎች ሰልፎች ማቆም የማይቻልበት ምክንያት በፍጹም አይገባውም ። በርግጥ ሰለዚሁ ጉዳይ የተጠየቁት የከተማው ከንቲባ ዩርገን ሽሮፕለር አሰቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ነው የሚናገሩት ።

« አዎ በርግጥ በመጀመሪያ በቀጥታ የምንሰጠው መልስ የሚያነሳው ጥያቄ ነው ። ከባቡር እንዲወርዱ አናደርግም ወይም ሰልፍ እንዳያካሂዱ አንከለክላቸውም ። ሆኖም ይህ ለዲሞክራሲ የሚከፈል ዋጋ ነው ። አክራሪ የሆኑ ኃይሎችን ማስተናገድ ግድ ነው ። ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲን የመሳሰሉ ፓርቲዎች እስካልታገዱ ድረስ ሁሉም መብታቸውን መሠረት በማድረግ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ ይችላሉ ። ስለሆነም እንዲህ ዓይነቱን የፖለቲካ ስብስባ ለመከልከል የሚያስችል ህግ ወይም ደንብ የለም ። »

እስካሁን ድረስ ጉዳዩን የሚከታተሉ ባለሥልጣናት በጥቃት አድራሾቹና በቀኝ አክራሪው ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ መካከል ስላለው ግንኙነት ግልጽ ማስረጃዎችን በመሰብሰብ ላይ ናቸው ። እነዚህ ማሰርጃዎች እስካልተገኙ ድረስ በጀመርመንኛው ምህፃር NPD የተባለው ይኽው ፓርቲ ሊታገድ አይችልም ። ያም ማለት ቀኝ አክራሪዎቹ በህጋዊ መንገድ ባልተመዘገቡ ማህበራት ውስጥ ይገኛሉ ። ስለዚህ አዋጪው መንገድ ዜጎች በግልጽ በቁርጠኝነት ቀኝ አክራሪዎችን ለመቃውም ታጥቀው መነሳታቸው መሆኑ ነው ተደጋጋሞ የሚወሳው ። ለምሳሌ ሬግንስቡርግ በተባለው ከተማ አፍቃሪ ናዚዎች በአንድ የይሁዲ ቡና ቤት ላይ ከባድ ጥቃት ካደረሱሰና ዝርፊያም ከፈፀሙ በኃላ ከ140 በላይ የቡና ቤት ባለቤቶች በመተባበር በየቡናቤታቸው በር ላይ ዘረኞች አይስተናገዱም የሚል ማስታወቂያ ለጥፈዋል ። የሬግንስቡርግ ነዋሪ ባለምግብ ቤቱ ማርቲን ዛይትልም ቀኝ አክራሪዎቹን በማይፈለጉበተ ቦታ መገኘታቸውን ለማሳየት የተለየ ነገር አደረጉ ።

Skinheads rufen "Sieg Heil"
ምስል AP

« የኔ ማስታወቂያ ጠቅሞኛል ። አኳሃናቸው ጥሩ ካልመሰለኝ ጓደኛዮ የውጭ ተወላጅ ነው የሚለውን ማስታወቂያየን ህዝቡ እንዲይይ አደርጋለሁ ። እናም በእንዲሁ ሁኔታ መልዕክቱን አሰተላልፋለሁ ። ይህ ነው መሆን ያለበተ በዚህ ላይም መወያየት አያሰፈልግም የቀኝ አክራሪዎች መገታት አለባቸው ። ማንም ሰው አቋሙን በግልፅና በፅናት ማሳየተ አለበት ። ይህን ነው ማለት የምችለው ። »

ቱርክ ጀረመናዊው ባለግሮሰሪ ደግሞ

« ሁሉም እለመታወሩን ማወቁና ና አንዳንዶችም የቀኝ አክራሪዎችን እንቅስቃሴዎች ተቃወመው መቆማቸውን ማየቱ ያስደስታል ። ሆኖም እነዚህ አናሳ የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው ። በዚህ ጉዳይ ውስጥ ግን ከህዝቡ አብዛኛው በጉዳዩ ይበልጥ ተሳታፊ መሆን ይገባቸዋል ።

የሙራት አስተያየት ድር ቢብር አንበሳ ያስር እንደሚባለው መሆኑ ነው ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ