ሽታይንብሩክ የ ኤስ ፕዴ እጬ ተወዳዳሪ
ሰኞ፣ መስከረም 21 2005ማስታወቂያ
የጀርመን ሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ በጀርመንኛው ምህፃር SPD የቀድሞውን የገንዘብ ሚኒስትር ፔር ሽታይንብሩክን በመጪው አመት ለሚካሄደው የጀርመን አጠቃላይ ምርጫ እጩ ተወዳዳሪ አድርጎ መምረጡን ዛሬ አስታውቋል ። SPD በታህሳስ ወር በሚያካሂደው ጉባኤ በእጩ ተወዳዳሪነነት በይፋ የሚሰየሙት የ65 አመቱ ሽታይንብሩክ በመጪው ምርጫ ከክርስቲያን ዲሞክራት ህብረት ፓርቲዋ አንጌላ ሜርክላ ጋር ነው የሚፎካከሩት ። ሽታይንብሩክ ከምርጫው በኋላ እንደተናገሩት በምርጫ ዘመቻ ወቅት የሚያተኩሩት በሜርክል የዩሮ ቀውስ አያያዝ ላይ ነው ። ስለ ሽታይንብሩክ ማንነትና በእጩ ተወዳዳሪነት እንዴት ሊመረጡ እንደበቁ የበርሊኑን ዘጋቢያችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ ጠይቄዋለሁ ።
ይልማ ኃይለ ሚካኢል
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ