ሽልማት ለቀድሞዉ የፖለቲካ እስረኛ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 7 2006ማስታወቂያ
ሽልማቱ በሁለቱ ሃገራት የሚኖሩ ወገኖችን ባለፈዉ ወር መጨረሻ አምስተርዳም ከተማ ላይ ባሰባሰበዉ ሕዝባዊ ስብሰባ ወቅት የተሰጠ ሲሆን፤ አቶ አበራ በፖለቲካዉ ሂደት ለከፈሉት መስዋዕትነትና ላሳዩት ጽናት የአክብሮትና ምስጋና መግለጫ እንደሆነም ተገልጿል። አቶ አበራ የማነአብ በ1986ዓ,ም መንግስት በጠራዉ የእርቅና ሰላም ጉባኤ ለመሳተፍ ወደአዲስ አበባ በሄዱበት ወቅት ተይዘዉ ለ17 ዓመታት ታስረዉ መቆየታቸዉ ይታወሳል። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሤ አቶ አበራን በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።
ገበያዉ ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ