ሹማኽር የደረሰበት አደጋ
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 21 2006ማስታወቂያ
« ፎርሙላ 1» በተሰኘው ፈጣን የአውቶሞቢሎች እሽቅድምድም ሰባት ጊዜ የዓለም ሻምፕዮን ጀርመናዊው ሚካኤል ሹማህር ትናንት በደረሰበት አደጋ ጀርመናውያን ተደናግጠዋል ። በፈረንሳዩ የአልፕስ ተራራ ትናንት በበረዶ ላይ ሲንሸራተት ራስ ቅሉ ላይ በደረሰበት አደጋ ክፉኛ መጎዳቱንና በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሃኪሞች ተናግረዋል ። የጀርመን መራሄ መንግሥት አንጌላ ሜርክልን ጨምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጀርመናውያን ሹማኽር በደረሰበት አደጋ ድንጋጤያቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው ። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል የበርሊን ነዋሪዎችን አነጋግሮ ቀጣይን ዘገባ ልኮልናል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ