1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶሪያ ግጭት፣ ሑከትና የዉጪዉ ጫና

ዓርብ፣ ኅዳር 8 2004

ፈረንሳይ በሶሪያ ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ስትጠይቅ፥ ቱርክ ሐሳቡን በገሚስ ተቀብላዋለች።ሩሲያ ግን ተቃዉማዋለች።

https://p.dw.com/p/RxMg
ተቃዋሚዉምስል picture-alliance/dpa

የሶሪያዉን ፕሬዝዳት የበሽር አል-አሰድን መንግሥት በመቃወም አደባባይ በተሠለፉና በመንግሥት ፀጥታ አስከባሪዎች መካካል የሚደረገዉ ግጭት ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።የመንግሥት ተቃዋሚዎች እንዳስታወቁት ዛሬ ከጁመዓ ሶላት በኋላ በተለያዩ ከተሞች የተሠለፉ ተቃዋሚዎች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር ተጋጭተዉ በትንሹ ሰባት ሰዉ ተገድሏል።የዉጪ ታዛቢዎች ወደ ሶሪያ እንዲገቡ የዓረብ ሊግ ያቀረበዉን ጥያቄ ሶሪያ በመርሕ ደረጃ መቀበሏን አስታዉቃለች።ፈረንሳይ በሶሪያ ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ስትጠይቅ፥ ቱርክ ሐሳቡን በገሚስ ተቀብላዋለች።ሩሲያ ግን ተቃዉማዋለች።ሥለ ሶሪያ ሁኔታ የጅዳ ወኪላችን ነብዩ ሲራክን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ነብዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ