ሶሪያ፥ የሩሲያና የዩናይትድ ስቴትስ ዕቅድ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 30 2005ማስታወቂያ
የሶሪያ ተፋላሚ ሐይላት የሚደራደሩበትን ሥልት የሚቀይስ ዓለም አቀፍ ጉባኤ እንዲደረግ የዩናይትድ ስቴትስና የሩሲያ ባለሥልጣናት ተስማሙ።የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ ሞሶኮ ዉስጥ ከሩሲያ መሪዎች ጋር ከተነጋገሩ በሕዋላ የወጣዉ የሁለቱ መንግሥታት የጋራ መግለጫ እንዳመለከተዉ ጉባኤዉ ምናልባት በሚቀጥሉት ሰወስት ሳምንታት ዉስጥ ይደረጋል። የአሜሪካዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ወደ ሞስኮ የተጓዙት ሩሲያ ለሶሪያ መንግሥት የምትሰጠዉን ድጋፍ እንድታቋርጥ ወይም እንድትቀንስ ለማግባባት ነበር።የፖለቲካ አዋቂዎች እንደሚሉት የኬሪ የመጀመሪያ አላማ ባይሳካም ከሞስኮ ባለሥልጣናት ጋር የደረሱበት ሥምምነት አስጊዉን የሶሪያ የርስ በርስ ጦርነት ለማቀላል መርዳቱ አይቀርም።በዚሕ ጉዳይ ላይ ከበርሊኑ ወኪላችንን ከይልማ ሐይለ ሚካኤል ጋር አጭር የስልክ ዉይይት አድርገናል።
ይልማ ሐይለ ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ