„ ሶሪያ ከአሳድ በኋላ“ የበርሊኑ ጉባኤ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 23 2004ማስታወቂያ
የሶሪያው ግጭት ተባብሶ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት በርሊን ውስጥ ሲመክሩ የቆዩት የሶሪያ መንግሥት ተቃዋሚዎች ሶሪያ ከአሳድ በኋላ የሚል አንድ ሰነድ ይፋ አድርገዋል ። ከ 6 ወራት ውይይት በኋላ ትናንት የወጣው የዚህ ሰነድ አላማም በሶሪያ የህግ የበላይነት በሰላማዊ መንገድ እንዲሰፍን መርዳት መሆኑን ጉባኤተኞቹ አስታውቀዋል ። የጉባኤው ተካፋዮች አለም ዓቀፉ ምህበረሰብ የሶሪያውን ፕሬዝዳንት የበሽር አል አሳድን የአንድ ፓርቲ አገዛዝ ስርዓት ለመጣል ተጨማሪ እገዛ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል ። ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ የተቃዋሚዎቹን ጅምር በማድነቅ አስተያየቱን ሰጥቷል ። ዝርዝሩን ይልማ ኃይለ ሚካኤል አዘጋጅቶታል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ