1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶማሊያና ጀርመን

ረቡዕ፣ ግንቦት 25 2002

ለተጨቆኑ ሰዎች የሚሟገት አንድ የጀርመን ድርጅት የሰላማዊ ሶማሊያውያን ዕልቂት እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል።

https://p.dw.com/p/Nfze
ሶማሊያና ጀርመን
ምስል AP

የድርጅቱ ተወካይ ኡልሪሽ ዴሊዩስ እንደገለጹት ከዕለት ወደዕለት የሰላማዊ ሶማሊያዊ ሞት እየጨመረ ነው። የሶማሊያን ጉዳይ በቅርበት ጥንደሚከታተል የገለጹት ተወካዩ ጀርመን በሰላማዊ ሶማሊያውያን ላይ የሚደርሰውን ግድያና መፈናቀል ለማስቆም ጥረት እንድታደርግ ጥሪ አቅርብዋል። በነገው ዕለት የሶማሊያ የሽግግር መንግስት ፕሬዝዳንት ወደ ጀርመን በመምጣት ከተጠባባቂው የጀርመን ፕሬዝዳንት ና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተርቬሌ ጋር እንደሚነጋገሩ የጠቀሱት ኡልሪሽ የሶማሊያው መሪ ሰላማዊ ሰዎችን ለመታደግ እንዲችሉ የጀርመን ባለስልጣናት ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ