ሶማሊላንድ እና ጸረ የባህር ላይ ውንብድና1 ሚያዝያ 2003ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 1 2003በሰሜናዊ ሶማልያ የምትገኘው ሶማሊላንድ ከጥቂት ቀናት በፊት አንድ በሱስ አስያዥ ዕጽ እና በወንጀል አንጻር በሚታገለው የተመድ መስሪያ ቤት ርዳታ በአንድ ነጥብ አምስት ሚልዮን ዩሮ ወጪ በርዕሰ ከተማ ሀርጌሳ የተሰራ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግበት ወህኒ ቤት ከፈተች።https://p.dw.com/p/RGeKምስል DW/Richard Loughማስታወቂያየቀድሞ የሶማልያ ፕሬዚደንት ሲያድ ባሬ እአአ በ 1991 ዓም ከስልጣን በተወገዱ ጊዜ ነጻነትዋን ያወጀችው እና ከዚያን ጊዜ ወዲህ ባካባቢው መረጋጋት የሰፈነባት ስርዓተ ዴሞክራሲን የምትከተለው ሶማሊላንድ የባህር ላይ ውንብድናን ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጎን በመሆን ለመታገል ቆርጣ መነሳትዋን አረጋግጣለች። DW