ስድስተኛዉ ፓትሪያርክ ተመረጡ21 የካቲት 2005ሐሙስ፣ የካቲት 21 2005የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስድስተኛ ፓትሪያርክ ምርጫ ዛሬ ተካሂዷል። በቤተክርስቲያኒቱ የስብሰባ አዳራሽ ሙሉ ቀን በተካሄደ የምርጫ ስርዓትም በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ተመርጠዋል።https://p.dw.com/p/17o4Pምስል DWማስታወቂያ ለምርጫዉ በእጩነት አምስት ሊቃነጳጳሳት የቀረቡ ሲሆን ከተሰጠዉ ስምንት መቶ ስድስት ድምፅ አምስት መቶዉን ማግኘታቸዉን የአስመራጭ ኮሚቴዉ ሰብሳቢ ገልፀዋል። የ 71 ዓመቱ ሊቀ ጳጳስ በዓለ ሢመታቸው የፊታችን እሁድ በመንበረ ጸባዖት ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚከናወን ተነግሮአል። ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ሸዋዬ ለገሠ አርያም ተክሌ