ስደተኞች ከሊባኖስ ወደ ጣልያን ተጓጓዙ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 27 2008ማስታወቂያ
የአንጌሊካዉያን አብያተ ክርስትያናት ፊደሪሽንና የቅዱስ ኢጂዲዮ ማኅበረሰብ በመተባበር አራት ኢራቃዉያንን ጨምሮ እና 97 101 የሶርያ ስደተኞችን ቤሩት ሊባኖስ ከሚገኝ የስደተኞች ጣብያ ወደ ጣልያን አስገቡ። የጣልያን መንግሥትና እንዚህ ተቋማት ባለፈዉ የካቲት ወር ላይ ዘጠና ስደተኞችን ከሊባኖስ ማስመጣታቸዉ ይታወቃል። የጣልያን መንግሥት ስደተኞቹ ወደ ጣልያን እንዲገቡ የቪዛ ፈቃድ ከመስጠት ዉጭ በፋይናንስ ረገድ ርዳታ እንደማይሰጥ ነዉ የተመለከተዉ። ጣልያን ሮም የሚገኘዉ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባዉን ልኮልናል።
ተክለዝጊ ገ/እየሱስ
አዜብ ታደሰ